Fana: At a Speed of Life!

ለሀረሪ ክልል አዲስ የምክር ቤት አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሀረሪ ክልል አዲስ የምክር ቤት አባላት በምክር ቤቱ አሰራር፣ በአባላት ስነ-ምግባር እና ደንብ ዙሪያ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል።
 
በስልጠናው ከስነ-ምግባር ደንቡ በተጨማሪ በምክር ቤቱ ተግባር፣ ስልጣንና ሃላፊነት ላይ አባላቱ ግንዛቤ እንዲያገኙ እንደሚደረግ ተገልጿል።
 
የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ወ/ሮ አዲስዓለም በዛብህ÷በ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ተወዳድረው ወደ ምክር ቤት የገቡ አባላት ህዝብን መሠረት ያደረጉ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
 
በተለይም ለህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡
 
አዲስ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አባላት በበኩላቸው÷ ህዝብ የጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት እና የማህበረሰቡን ህይወት ለማሻሻል የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
 
በመድረኩ ላለፉት 6 ዓመታት የምክር ቤቱ አባል በመሆን ላገለገሉ አባላት ሽኝት ከተደረገ በኋላ በተያዘው ሳምንት መጨረሻ አዲሱ የክልል ምክር ቤት ምስረታውን እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
 
በተሾመ ኃይሉ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.