Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎች ኢላማቸውን የመቱ መሆናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎች ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎች ላይ ብቻ እንደሆነና ኢላማቸውን የመቱ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገጽ ባወጣው መግለጫ፤የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸውን የአየር ድብደባዎች በተመለከተ የተዛባ ግንዛቤ ቢኖርም፣ በተቃራኒው ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው ብሏል።
የመከላከያ ሠራዊት የሚያከውናቸው እነዚህ ሥራዎች የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን እና ሌሎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ የሚጠቀምባቸውን እና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ያለመ ነው ሲልም አስታውቋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.