Fana: At a Speed of Life!

ነገና ከነገ ወዲያ በኢትዮጵያና ኬኒያ ድንበር የእንስሳት ክትባት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬኒያ እና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢዎች የሚካሄደውን የእንስሳት ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ በሞያሌ ከተማ ውይይት ተካሄደ፡፡
ውይይቱም÷ በክፍለ አህጉራዊ የአርብቶ አደር ኑሮ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት አማካኝነት ድንበር ዘለል ተዛማች የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከል በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢዎች በሚካሄደው የእንስሳት ክትባት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በዚሁ መሠረት÷ በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አስተባባሪነት በኢትዮጵያ እና በኬኒያ ድንበር አካባቢዎች የእንስሳት ክትባት ዘመቻው ነገ እና ከነገ ወዲያ በይፋ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.