Fana: At a Speed of Life!

በዞኑ የበጎ ፈቃድና የዜግነት አገልግሎት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የበጎ ፈቃድና የዜግነት አገልግሎት በህብረተሰቡ ህይወት ላይ ውጤት ያለው ለውጥ እያመጣ መሆኑን የባሌ ዞን ህጻናት፣ ሴቶችና ወጣቶች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የዞኑ ህጻናት፣ ሴቶችና ወጣቶች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ህንዲያ ሁሴን ለኢዜአ እንደገለጹት÷ በየጊዜው እየተካሄዱ የሚገኙ የበጎ ፈቃድና የዜግነት አገልግሎት ስራዎች በህብረተሰቡ ኑሮ ላይ ውጤት ያለው ለውጥ እያመጡ ነው፡፡
ባለፈው ክረምት የበጎ ፈቃድና የዜግነት አገልግሎት በዞኑ 12 ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ 300 ሺህ የሚሆኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ተናግረዋል፡፡
በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የ398 አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት መልሶ ግንባታና እድሳት፣ የአረጋዊያን እንክብካቤና ለ65 ሺህ ችግረኛ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የማድረግ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
ከበጎ ፈቃደኞቹ 602 ዩኒት ደም መሰብሰቡንና በሀገር ህልውና እየተሳተፉ ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊትና የጸጥታ አካላት ከ600 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓልም ተብሏል፡፡
በመርሀ ግብሩ በተከናወኑ የሰብአዊ ድጋፍና የልማት ስራዎች ከ1 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸውንና ከመንግስት ካዝና ይወጣ የነበረን ከ160 ሚሊየን ብር በላይ ለማዳን መቻሉንም ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.