Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ የውሃ ብክነትን መቀነስ የሚያስችል ስምምነት ፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃ ብክነትን በመቀነስ የውሃ ስርጭቱን ማስተካከል የሚያስችል ስምምነት ማያ ኮርፖሬሽን ከተባለ የሉዘንበርግ ድርጅት ጋር ስምምነት አድርጓል፡፡
 
የከተሞች ውሃ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ሁለተኛው ምዕራፍ አካል የሆነው ይህ ስምምነት÷አጠቃላይ ወጪው 8 መቶ ሚሊየን 487 ሺህ 107 ብር መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
ፕሮጀክቱ በአራት ዓመት ከ2 ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ስምምነቱ በጉርድ ሾላ እና ለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በተለዩ 25 ቀጠናዎች ማለትም በየካ አባዶ፣ የካ አያት፣ ፋኑኤል፣ ቦሌ አያት እና ቦሌ አራብሳ አከባቢ በሚገኙ የውሃ ስርጭት መስመሮች ላይ የዲዛይን ስራ በመስራት እያጋጠመ ያለውን የውሃ ብክነት በመቀነስ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል ነው፡፡
 
ፕሮጀክቱ ከ37 ሺህ 500 በላይ ደንበኞች በሚገኙበት አካባቢዎች ያረጁ የውሃ መስመሮችን፣ የውሃ ቆጣሪዎችንና መገጣጠሚያዎችን በመቀየር የደንበኞችን መረጃ በማዘመን እና የዕውቀት ሽግግርን በማድረግ የውሃ ስርጭት መረቡን የሚስተካክል እና ሲባክን የነበረውን ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያድን ነው ተብሏል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.