Fana: At a Speed of Life!

ፈሳሽ ማዳበሪያው የአፈር ማዳበሪያ አማራጭ ሆኖናል – አርሶ አደሮች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞረት እና ጅሩ ወረዳ ከዞኑ የተውጣጡ አርሶ አደሮች እና የግብርና ባለሞያዎች የገብስ እና ስንዴ ማሳ ጉብኝት አደረጉ።

በወረዳው ተግባራዊ የተደረገው እና ”ከውጭ የሚመጣውን የአፈር ማዳበሪያ ይተካል” የተባለውን የተፈጥሮ ፈሳሽ ማዳበሪያ የተጠቀሙ አርሶ አደሮች ማሳም ተጎብኝቷል።

የፈሳሽ ማዳበሪያው በሀገር ደረጃ ተከስቶ በነበረው የአፈር ማዳበሪያ እጥረትን ለመፍታት አስተዋፅኦ የነበረው መሆኑን ያነሱት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የቀድሞዋ የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ መሠረት ሀይሌ ÷ የግብርናው ዘርፍን ለማሳደግ መሰል ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባልም ብለዋል።

የፈሳሽ ማዳበሪያው የፈጠራ ባለቤት አቶ ከበደ ላቀው እንዳሉት ÷ ድርጅቱ ከውጭ የሚገባ ማዳበሪያን ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም አቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን ባሳለፍነው ዓመት 112 ሺህ ሊትር በላይ ፈሳሽ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ÷ በሞረት እና ጅሩ ወረዳ ደግሞ 21 ሺህ ሊትር ጥቅም ላይ መዋሉ ተገልጿል።

አርሶ አደሮቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት አስተያየት ÷ ፈሳሽ ማዳበሪያው የአፈር ማዳበሪያ አማራጭ ሆኖናል ብለዋል፡፡

በኤልያስ ሹምዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.