Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ፀረ ሽምቅ ልዩ ኃይል አባላት አስመርቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ለ2ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ፀረ ሽምቅ ልዩ ኃይል አባላት አስመርቋል፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የተገኙ ሲሆን ÷በመድረኩ መንግስታችን የተናገረውን የሚፈጽም፤ የማይፈፅመውን የማይናገር የተግባር መንግስት ነው ብለዋል።

የጸጥታ ኃይሉ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በክልሉ በመተከልና ካማሽ ዞን የሚታየውን መፈናቀልና የሰው ህይወት ማለፍ በመግታት ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የክልሉ የሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዩት አልቦሮ÷ ሀገር አቀፍ የፖሊስ መርሖዎች በመጠቀም ፣ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት አሸባሪው ህወሓት ቡድን፣ ሸኔ እና በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የእነሱ ተላላኪዎችን በአጭር ጊዜ በመደምሰስ የተያዘውን የብልጽግና ጉዞ ከዳር እንዲደርስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የፖሊስ አባላቱ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባዋል ብለዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ኮማንደር አብዱላዚም መሀመድ በበኩላቸው÷የፖሊስ አባላቱ ክልላቸውን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ዲን ኮማንደር አዳሙ እጀታ ደግሞ÷ ሰልጣኞቹ የፖሊስ አባላት ባገኙት ክህሎት ክልላቸውንና ሀገራቸውን በብቃት ሊያገለግሉ እንደሚገባ ማመላከታቸውን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.