Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለጅቡቲ ያበረከተችው ችግኝ የሃገራቱን ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክራል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለጅቡቲ ያበረከተችው የአረንጓዴ አሻራ አካል የሆነው ችግኝ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን የጅቡቲ የግብርና ሚኒስትሩ ሞሃመድ አዋሌ ገለጹ፡፡

ጅቡቲ ከኢትዮጵያ በመጀመሪያው ዙር የተበረከተላትን 40 ሺህ ችግኞች መተከል መጀመራቸውንም ነው የገለጹት፡፡

ኢትዮጵያ ጅቡቲን ጨምሮ የጎረቤት ሀገራትን የአረንጓዴ አሻራ አካል በማድረጓም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ሃገራቱ ወንድማማች ህዝቦች ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ÷ የተበረከተው ችግኝ ታሪካዊ የሆነውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ እስከ 200 ሺህ ችግኝን ለጂቡቲ ለመስጠት ማቀዷ የተጠቀሰ ሲሆን÷ የመጀመሪያው ዙር ችግኝ ከሳምንት በፊት ነበር ከድሬዳዋ ወደ ጂቡቲ የተላከው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፈው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 6 ቢሊየን ችግኞችን በሀገር ውስጥ የተከለችው ኢትዮጵያ 1ቢሊየን ችግኞች ደግሞ ለጎረቤቶቿ ማዘጋጀቷን በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.