Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የፖሊዮ ክትባት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ከነገ ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን የከተማዋ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በቢሮው የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት ዳይሬክተር ቤተልሔም ታየ የክትባት አሰጣጡን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ÷ በመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ከ555 ሺህ በላይ ህፃናት ይሰጣል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ከታህሳስ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገ ዳሰሳ÷ የፖሊዮ በሽታ አምጭ ተህዋሲ መኖሩ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
በዚሁ መሠረትም÷ የመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከነገ ጥቅምት 12 እስከ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ቤት ለቤት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
ክትባቱን የሚሰጡት የጤና ባለሙያዎች ለኮቪድ መከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ ጠቁመው÷ ወላጆችም ልጆቻቸውን በተጠቀሱት ቀናት ማስከተብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የሁለተኛው ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚሰጥ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.