Fana: At a Speed of Life!

ለግዳጅ ተሰማርተው ጥሩ አፈፃፀም ላሳዩ የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል አባላት የማዕረግ እድገት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በተለያዩ ቦታዎች ለግዳጅ ተሰማርተው ጥሩ አፈፃፀም ላሳዩ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላት የማዕረግ እድገትና ሽልማት ሰጡ።

በአቶ ሙስጠፌ መሃመድ የተመራ ከፍተኛ የክልሉ ልዑኩ ወደ ተለያዩ ግዳጆች ተሰማርተው በድል የተመለሰውን የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል አባላትን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱም ጥሩ አፈፃፀም ላሳዩ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላት የማዕረግ ዕድገትና ሽልማት ተሰጥቷል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ዋና አዛዥ ም/ኮ መሀመድ አህመድ በስነስርዓቱ ላይ ÷ በተለያዩ ቦታዎች ሀገር ለማዳንና ሰላምን ለማስከበር በፈፀማቹት ጀግንነት ህዝባቹ ኮርቶባቿዋል ፤ ወታደር ትናንት ከግዳጅ ሲመጣ ፣ ነገም ለግዳጅ መዘጋጀት የወታደር ስራ ነው ብለዋል።

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙበሽር ዱበድ በበኩላቸው ÷ የክልሉን ልዩ ሀይልና የፀጥታ ተቋማት ለማጠናከር በሰፊው ተሰርቷል አሁንም የበለጠ ይሰራል ብለዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ሙስጠፌ ከለውጡ ማግስት ልዩ ሀይሉ ይበተናል የሚል አሉባታ ፀረ ለውጥ በሆኑ ሰዎች ሲናፈስ ነበር፣ ነገር ግን ባለፉት ሦስት አመታት እናንተ በሰራችሁት ስራ ህዝባቹና ሀገራቹ ኮርቶባቹዋል ብለዋል።

አሁን ላይ እንደ ሀገር እና እንደ ክልል ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግረናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ይህን አዲስ ምዕራፍ ለማደናቀፍ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ አካላት በመኖራቸው ህግን ለማስከበር በሚደረገው ስራ የእናንተ ሚና ከፍተኛ ነው ማለታቸውን የሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.