Fana: At a Speed of Life!

የንግድ ውድድር ፣ የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን እና የምርት ገበያ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር ተዋሃዱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ የተቋማቱ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር መዋሃድ ለስራ መቀላጠፍ የሚያበረክተው ሚና የላቀ ነው ብለዋል፡፡

የፌደራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን መስከረም 2014 ዓ.ም በወጣ አዋጅ መሰረት ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተጠሪ የነበሩ ንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን እና የምርት ገበያ ተቋማት ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር መዋሃዳቸው የተሻለና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያግዝ ተነስቷል፡፡

ሚኒስትሩ ከሁለቱ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ጋር በተወያዩበት ወቅት የተቋማቱ መዋሃድ በስራቸው ላይ ምንም አይነት እንቅፋት እንደፈማይፈጥርና ይልቁንም የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ እንደሚረዳ ገልፀዋል፡፡

የሁለቱ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ስራቸውን ከመቼውን ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ለማከናወን በትጋትና በመተባበር መስራት እንደሚጠበቅባቸው መናገራቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.