Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የዓለም አቀፍ አድቮኬሲ አገልግሎት የወርቅ ተሸላሚ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኢንቨስትመንትን በማጠናከርና በማስፋፋት ላከናወነው የላቀ አገልግሎት የዓለም አቀፉ የአድቮኬሲ አገልግሎት የወርቅ ተሸላሚ መሆኑ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የዓለም አቀፉ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ አሶሴሽን (WAIPA) እንዲሁም የአለም ባንክ ቡድን በጥምረት የሚያዘጋጁትን ዓለም አቀፋዊውን የኢንቨስትመንት ማጠናከሪያና ማስፋፊያ አገልግሎት (Strengthening IPA Advocacy Services) የዓመቱ የወርቅ ተሸላሚ ሆኗል።

ሽልማቱ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጀት የንግድና የልማት ኰንፍረንስ (UNCTAD ) ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ነው ለኮሚሽኑ ሽልማቱ የተበረከተለት።

በበይነ መረብ በተካሄደው የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ተቋማቸውብሎም አገራቸው በመሸለማቸው የደስታ መግለጫ ንግግር አድረገዋል።

ሽልማቱ ለሀገራችን ኢንቨስትመንት ሴክተር እድገት፣ አለም አቀፋዊ እይታ እና ተደራሽነት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት መገለጹን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.