Fana: At a Speed of Life!

በታማኝነት መትጋት ትውልድንና ሀገርን ለማቅናት መነሣትን ያሳያል- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በታማኝነት መትጋት ለትውልድ ማሰብን፣ ሀገርን ለማቅናት መነሣትን ያሳያል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
ባለፈው ዓመት ታማኝ ግብር ከፋዮች ሥራቸውን ሲሠሩ ሌብነትንም እንዲዋጉ ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውሰው÷ ጥሪውን ለተቀበሉት ቆራጦች በዛሬው ዕለት ልዩ እውቅና ሰጥተዋል።
በዚሁ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ለእውቅና የበቃችሁ ግብር ከፋዮችን ሀገር ታመሰግናችኋለች ብለዋል።
በሚቀጥሉት ዓመታትም ሀገርና ትውልድን አክብረውና አስቀድመው አርዓያነታቸውን ወደ ሌሎች እንዲያጋቡ የአደራ መለዕክትም አስተላልፈዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.