Fana: At a Speed of Life!

ቱሪዝሙን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ዘርፉን ማነቃቃት እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቱሪዝም አገልግሎትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ዘርፉን ማነቃቃት እንደሚገባ ተጠቆመ።
የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው ሲፖዚየም ላይ÷
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአገር ልማት ጥናት ኮሌጅ የቱሪዝም መምህር ዶክተር ተስፋዬ ዘለቀ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።
በፅሁፋቸውም÷ ኮቪድ-19 በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ያሳደረውን ጫና ለመቀነስ መዳረሻዎችን በስፋት ማስተዋወቅ፣ በቴክኖሎጂ መደገፍ፣ አማራጭ የቱሪዝም ምርት ሽያጮችን መጠቀም ያስፈልጋል ነው ያሉት።
በኢትዮጵያ የቱሪዝም አገልግሎትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ዘርፉን ማነቃቃት ይገባል ብለዋል ዶክተር ተስፋዬ።
በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የተከሰተው የሰላም እጦት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተጨምሮ በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ጫና ማሳደሩን ጠቅሰው÷ አማራጭ መዳረሻዎችን ማስተዋወቅ ያስፈልጋል ብለዋል።
አስጎብኝ ድርጅቶች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የቱሪስት ሃብቶችን አማራጭ አድርገው ማቅረብ እንደሚገባቸውም ነው የገለጹት።
በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና ብቃት ማረጋገጥ ዳሬክተር አምደማሪያም ማሞ በበኩላቸው÷ በከተማዋ የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን በተለያዩ አማራጮች ለማስተዋወቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.