Fana: At a Speed of Life!

የፖሊዮ ክትባት በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የፖሊዮ ክትባት በድሬዳዋ አስተዳደር ፣በሐረሪና በደቡብ ክልል እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ዞንና በሌሎች አካባቢዎች መሰጠት ተጀምሯል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር ለቀጣዮቹ አራት ቀናት ቤት ለቤት የሚሰጠውን የክትባት ዘመቻ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ አስጀምረውታል፡፡

በተመሳሳይ ክትባቱ በሃረሪ ክልል እየተሰጠ ሲሆን ÷ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብሳ ኢብራሂም፤ የፖሊዮ በሽታ ሥርጭትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ክትባት እየተሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

 

 

እንዲሁም በደቡብ ክልል ለቀጣዮቹ 4 ቀናት በዘመቻ መልክ የሚሰጠው የፖሊዮ ክትባት በይፋ ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የጤና የሚኒስር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ፣የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ ፣ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ እና ጥሪ የተደረገላቸው የፌደራል ፣የክልልና የዞን ተወካዮች ወላጆችና ህጻናት ተገኝተዋል።

በክልሉ በአጠቃላይ እድሜያቸው አምስትና ከዛ በታች የሆኑ ከ3 ሚሊየን በላይ ህጻናት የክትባቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪ የፓሊዮ ክትባት በሰሜን ሸዋ ዞን መሰጠት ተጀምሯል፡፡

ክትባቱን ለመስጠት በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የዞኑ ጤና መምሪያ ምክትል ሀላፊ ወይዘሮ ፀዳለ ሰሙ ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ ክትባቱ ከዛሬ ጥቅምት 12 እስከ 15 ቀን 2014ዓ.ም ድረስ የሚቆየው መሆኑ ታውቋል፡፡

እድሜያቸው አምስትና ከዛ በታች የሆኑ ህጻናትም የክትባቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ በዚህም ወላጆች፣ትምህርት ቤቶችና ሌሎችም ተቋማት ህጻናትን እንዲያስከትቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በከድር ሽምሽዲንና በአላዩ ገረመው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.