Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በበጋ መስኖ15 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ ለመሸፈን ታቅዷል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የግብርና ዘርፉን ማሻሻል ለክልሉም ሆነ ለሀገር እድገትና ብልፅግና ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት ያሻል ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ገለጹ፡፡
በበጋ ወራት የሚመረተው የመስኖ ስንዴ በምግብ እራስን የመቻል አቅም እንደሚያሳድግ የጠቆሙት ኃላፊው÷ በዘንድሮው የበጋ መስኖ መርሃ ግብርም በክልሉ በ172 አውታሮች 15 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ ሰብል ለመሸፈንና ከዚህም 525 ኩንታል ስንዴ ለማግኘት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ከ 1 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በአፈር መሸርሸር እንደተጎዳ የገለጹት አቶ ኡስማን÷ እንደዚህ ዓይነት ችህግሮችን ለመከላከልም በ2014 የአረንጓዴ አሻራ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል፡፡
በዚሁ መሠረትም ለምግብነት የሚውሉ ደኖችን ጨምሮ 927 ሚሊየን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን የጥምር ደን እርሻ ችግኞችን እና 834 ነጥብ 3 ሚሊየን መደበኛ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ገልጸዋል፡፡
በክልሉ የቡና ምርትን ማሳደግና የገበያ ትስስር መፍጠር እንዲሁም በቴክኖሎጂ መደገፍ በአመቱ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ በመሆኑ÷ ይህን ለማሳካት ሁሉም ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ኃላፊው አሳስበዋል፡፡
በጥላሁን ይልማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.