Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የ12ኛ ክፍል ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ለማስፈጸም በከተማ አስተዳደሩ ከተዋቀረው የኮማንድ ፖስት አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በከተማ ደረጃ በስኬት እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል ያሉት የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ አንዳንድ የግል ትምርት ቤቶች ግን እስካሁን አድሚሽን ካርድ ለተማሪዎች አለማድረሳቸውን ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በ62 የፈተና ጣቢያዎች 36 ሺህ 415 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ፈተና እንደሚወስዱና ይህንንም የሚመሩና የሚያስተባብሩ 2 ሺህ 600 የፈተና አስፈጻሚዎች ምልመላ መካሄዱን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.