Fana: At a Speed of Life!

ህዝበ ምዕምኑ በፀሎት እንዲበረታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት12፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሰላም እጦትና አለመረጋጋት ሳቢያ በንፁሃንና በሀገር ደህንነት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እንዲያበቃ ህዝበ ምዕመኑ ፀሎትና ተማፅኖውን እንዲያበረታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በየዓመቱ ጥቅምት 12 የሚካሄደውን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ አስጀምረዋል፡፡

ምዕመናንና ሀገርን መጠበቅ እንዲሁም ሰላምን መሻት የቅድስት ቤተክርስቲያን ግብር እና ተልዕኮ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው÷ ለወገን ሰላም የሃይማኖት አባቶችና አብያተ ክርስቲያናት ተግተው እንዲፀልዩ አሳስበዋል፡፡

ሰላም ለመንፈሳዊም ሆነ ለዓለማዊ እንቅስቃሴ እጅጉን አስፈላጊ ነው ያሉት ፓትሪያርኩ÷ በአገራችን በተወሰኑ አካባቢዎች ባለው የሰላም እጦት ሳቢያ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እንዲያበቃ ምዕመኑ ፀሎትና ልመናውን እንዲያጠናክር ጥሪ ማቅረባቸውን ከኤ ኤም ኤን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.