Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ ስምንት ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 8 ሚሊየን 450 ሺህ 464 መድረሱን የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) አስታውቋል።
አሁን ላይ በአህጉሪቱ በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 216 ሺህ 264 ደርሷል ነው የተባለው።
7 ሚሊየን 831 ሺህ 265 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸውም ተገልጿል።
ደቡብ አፍሪካ ፣ ሞሮኮ ፣ ቱኒዚያ እና ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ቫይረሱ በብዛት ከተሰራጨባቸው ሃገራት መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው።
ደቡባዊ የአፍሪካ ሃገራት በርካታ ቁጥር ያላቸው የቫይረሱ ተጠቂዎች የሚገኙባቸው ሲሆን፥ ሰሜን እና ምስራቅ አፍሪካ ደግሞ በተከታይነት ተቀምጠዋል።
በሌላ በኩል በመካከለኛዉ አፍሪካ ዝቅተኛ የቫይረሱ ስርጭት ታይቷል ሲል ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
በአመለወርቅ ደምሰው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.