Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ስራን ለማሳካት የክተት አዋጅ በማድረግ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል – የክልሉ ትምህርት ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር አጠቃላይ የትምህርት አጀማመር እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት አተገባበር ሒደት ላይ በአርባምንጭ ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

የደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ÷ትምህርት ስራ ሁሉንም የሚመለከት በመሆኑ ቅንጅታዊ ስራ ያስፈልጋል ብለዋል።

ከተማሪ ቅበላ ጀምሮ የመማር ማስተማር ስራዎችን በማሳካት ውጤት እንዲመጣ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።

በክልሉ ከታቀደው እስካሁን ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ 80 ከመቶ ተማሪዎች መመዝገባቸውም ተገልጸዋል።

የደቡብ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው÷ የሰው ኃይልን በብቃትና በቅንጅት በመምራት ሁሉም ለትምህርት ስራ ባለቤት እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የትምህርት ስራ ድንበር የለሽ በመሆኑ ሁላችንም የተማረ ስው ኃይል በመፍጠር ለሁሉ አቀፍ እድገትና ለውጥ መረባረብ እንደሚያስፈልግ አሳሰበዋል።

በማቴዎስ ፈለቀ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.