Fana: At a Speed of Life!

የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ በመፍጠር የስራ አጥነት ችግርን ለማቃለል ይሰራል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ በመፍጠር የስራ አጥነት እና የኑሮ ወድነት ችግርን ለማቃለል የሚሰራ መሆኑን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ።

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች በቀጣይ በሚያከናወኑት ስራ ላይ ያተኮረ ውይይት እያደረጉ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል÷ “በኢትዮጵያ የተረጋጋ ማክሮ-ኢኮኖሚ በመፍጠር የስራ አጥነት እና የኑሮ ውድነት ችግርን ለማቃለል በትኩረት ይሰራል” ብለዋል።

በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ አመልክተው÷ በተለይም የስራ አጥነት ችግርን ለማቃለል እንደሚሰራ ጠቅሰዋል።

“ዜጎች ባላቸው ክህሎት በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ በመሰማራት ውጤታማ ስራ እንዲያከናውኑ ይደረጋል” ያሉት ሚኒስትሯ÷ በኢትዮጵያ በእውቀትና ክህሎት ተወዳዳሪ እንዲሁም ምርታማ የሰው ኃይል መፍጠር ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚሆን አመልክተዋል።

የስራ አጥነትን ችግር በማቃለል እና እየተባባሰ የመጣውን የኑሮ ውድነት ችግር ለመፍታት አዳዲስ አሰራሮችን በመፍጠር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

የኢንዱስትሪ ሰላምን ለማረጋገጥ በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ሁለቱንም ተጠቃሚ የሚያደርጉ አሰራሮች መፍጠር እንደሚያስፈልግ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.