Fana: At a Speed of Life!

ቢሮው በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የዓይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቢሮ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አድርጓል።
በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከተፈናቀሉት 63 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት እናቶችና ህፃናት መሆናውን የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ በይዲ ሙንዲኖ ተናግረዋል፡፡
በየአመቱ የሚከሰተው የኦሞ ወንዝ ሙላት በዘላቂነት ችግሩ የሚፈታበት ሁኔታ እስኪመቻች ድረስ÷ ጊዜያዊ ድጋፍ ማድረግ ተገቢ መሆኑንም ነው ኃለፊዋ ያብራሩት፡፡
የዳሰነች ወረዳ ተፈናቃዮች ቤት ንብረታቸውን እዛው ጥለው የወጡ በመሆኑ÷ ቢሮው ጊዜያዊ ችግራቸውን የሚፈቱበት ይሆናል ያላቸውን የዱቄት፣ የዘይት፣ የሩዝ፣ የስኳርና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉን ከደቡብ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ኦሞ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ናኪያ ናቁሳ እንዳሉት÷ በየዓመቱ የሚከሰተውን መፈናቀል በተለይ ለእናቶችና ህፃናት አስቸጋሪ በመሆኑ የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቢሮ በፍጥነት እርዳታን ይዞ በመምጣቱ ምስጋናን እናቀርባለን ብለዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ ኤፍሬም ወርቁ በበኩላቸው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመው÷ የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ቀደም ሲል ለከብቶች መኖ የሚሆን 4 ሚሊየን ብር እንዲሁም አሁንም በአካል በመገኘት 4ሚሊየን ብር የሚያወጣ የዓይነት ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.