Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሚስራ አብደላ የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው ጉባኤ ወይዘሮ ሚስራ አብደላን በድጋሚ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።

ምክር ቤቱ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ለክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርነት እጩ ሆነው የቀረቡለትን የወይዘሮ ሚስራ አብደላ ሹመት መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አማካኝነት ቃለ-መሐላ የፈፀሙ ሲሆን በዚህም ህዝብን በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል ቃል መግባታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ የቀረበለትን የስራ አስፈጻሚዎች ሹመት መርምሮ አፅድቋል።

በዚህ መሰረትም፡-

1. ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ
የክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ

2. ወይዘሮ ፈሪሃ መሀመድ የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

3. አቶ አዩብ አህመድ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ

4. ዶክተር ኢብሳ ሙሳ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ

5. ወይዘሮ ጠይባ አብደላ የክልሉ ትራንስፓርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ

6. ወይዘሮ ደሊላ ዩሱፍ የክልሉ ሴቶች ፣ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

7. አቶ በቀለ ተመስገን የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

8. አቶ ሙክታር ሳሊህ የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

9. አቶ ተወለዳ አብዶሽ የክልሉ ባህል ፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

10.አቶ ኢስማኤል ዩሱፍ የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ

11. ወይዘሮ ሰሚራ ዩሱፍ የኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

12. አቶ ጥላሁን ወደራ ጎበና የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.