Fana: At a Speed of Life!

ህብረተሰቡ የኮቪድ-19 ክትባትን በመውሰድ ወረርሽኙን እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 12፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እስካሁን የኮቪድ-19 ክትባትን የወሰደው የህብረተሰብ ክፍል አራት በመቶ ያህሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በተያዘው ዓመት እስከ ጥር ወር ድረስ 20 በመቶ የሚሆነውን ህብረተሰብ ለመከተብ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በሚኒስቴሩ የክትባት ፕሮግራም አማካሪ የሆኑት ወይዘሮ ሊያ ወንድወሰን ከፋናብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የቫይረሱ ስርጭት አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰው በዚሁ ከቀጠለ ከጤና ተቋማት አቅም በላይ ሊሆን እንደሚችል ነው ያነሱት።

ፋይዘር የተሰኘውን ክትባት ጨምሮ ሌሎች የክትባት ዓይነቶችን የማስገባት ስራ እየተሰራ መሆኑን አማካሪዋ ተናገረዋል።

ሦስት የክትባት ዓይነቶች በሁሉም የመንግስት ጤና ተቋማት በነፃ እየተሰጠ ሲሆን÷ እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ የሆኑ ሁሉ ማግኘት ይችላሉ ነዉ የተባለዉ።

ህብረተሰቡ ክትባቱን በፈቃደኝነት መውሰድ እንዳለበት ያሳሰቡት ወይዘሮ ሊያ÷ ወረርሽኙ በዚሁ ከቀጠለ ከጤና ፖሊሲው አንፃር ክትባቱን መውሰድ አስገዳጅ ሊሆን እንደሚችልም ተናግረዋል።

እስካሁን በኢትዮጵያ ከ 3 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ሰዎች ክትባት መውሰዳቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

በዙፋን ካሳሁን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.