Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለግብርናዉ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለባት ምሁራን አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምግብ እራስን ለመቻል ኢትዮጵያ ለግብርናዉ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለባት ምሁራን አሳስበዋል፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የግብርና ተመራማሪዉ ዶክተር ኤርሚያስ አባተ እንደተናገሩት÷ ግብርና ለሀገራችን የሁሉም ነገሮች አንቀሳቃሽ መሰረት ነዉ ፡፡

ለዚህም በፈተናዎች የተከበበችዉ ኢትዮጵያን ለመታደግ፤ በምግብ እራሳችንን ለመቻል መንግስት ለግብርና ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የግብርና እና ምርምር መምህሩ ዶክተር ተስፋዬ መላክ በበኩላቸዉ÷ አሁን ኢትዮጵያ ከመቼም ጊዜ በላይ በምግብ እራሷን መቻል ያለባት ወቅት ላይ በመሆኗ የግብርናዉ መዘመን አንገብጋቢና ተቀዳሚ የመንግስት ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ለዚህም መንግስት አበረታች ዉጤት የታየባቸዉን የክላስተር ስራዎች ማጠናከር አስፈላጊ ስለመሆኑ አመላክተዋል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት ምሁራን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ የታደለቻቸዉን ሀብቶች ባግባቡ ማቀናጀትና መተግበር ከቻለች ሰፊ የቆላ እርሻዎቿ እና አመቱን ሙሉ የሚፈሱት ወንዞቿ ባግባቡ ከተሰራባቸዉ ዉጤት እንደሚያስገኙ ያላቸዉን እምነት ገልፀዋል።

ይህ ደግሞ ምዕራባዉያን የሚመፃደቁበትን ስንዴ ከመለመን የሚያወጣ እና ሉዓላዊነትን በአስተማማኝ መልኩ ለማረጋገጥ ከጥገኝነትም ለመላቀቅ የሚያስችል የመጀመሪያዉም የመጨረሻዉም አማራጫችን ነዉ ሲሉም በአፅኖት አስረድተዋል።

በሙሀመድ አሊ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.