Fana: At a Speed of Life!

ከ46 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ባሳለፍነው ሳምንት ከ46 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ባሳለፍነው ሳምንት ባደረገው ክትትል 43 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊየን ብር በላይ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች በ13 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ፣ አቃቂ እና ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ ÷በቅደም ተከተላቸው 13 ሚሊየን፣ 12ነጥብ 1 ሚሊየን እና 9ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በመከላከያ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ መያዛቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፣ መድሀኒት ፣ ጫት ፣ አደንዛዥ እጽ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ የጦር መሳሪያዎችና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.