Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስቴር በቦረና በድርቅ ለተጎዱ እንስሳት የሚውል 77 ሺህ ቤል ሳር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በቦረና 11 ወረዳዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተ ድርቅ በአካባቢው የሚገኙ እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል።

ይህንን ጉዳት ለመከላከልም የተለያዩ አካላት የእንስሳት መኖ ወደ አካባቢው እየላኩ የሚገኝ ሲሆን ÷ የግብርና ሚኒስቴርም በዛሬው ዕለት 77 ሺህ ቤል ሳር ድጋፍ አድርጓል።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሳ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ድጋፉ የእንስሳቱን ጉዳት የሚቀንስ እንደሆነ ገልጸው ÷ በቀጣይም ሌሎች መፍትሄዎችን ለማስቀመጥ የጥናት ቡድን ወደ ስፍራው መላካቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም ድርቅ በሚከሰት ሰዓት እንዲህ አይነት የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በአካባቢው የመኖ ማካማቻ መጋዘን በስፋት ሊኖር እንደሚገባ ያነሱት የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶክተር ቶማስ ቸርነት ÷ ቀደም ብሎ መኖዎችን በማከማቸት ጉዳቱን መከላከል ይገባል ብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የግብርና ሚኒስቴር እየሰራቸው ያሉ ፕሮጀክቶች እንዳሉ የገለጹት ዶክተር ፍቅሩ ÷ እነሱን በማጠናከር አካባቢው ላይ የመኖ ምርት እንዲኖር መስራት እንደሚገባም ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊና የእንስሳት ልማት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ቶሌራ ደበላ በበኩላቸው ÷ በዞኑ የሚከሰተውን ድርቅ በዘላቂነት ለመከላከል የተለያዩ የውሃ ፕሮጀክቶች ተቀርጾ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዘመን በየነ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.