Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ በጅግጅጋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በጅግጅጋ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡
 
በጉብኝት መርሃ ግብሩ የክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱረህማን ኢድን እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችም ተሳትፈዋል፡፡
 
በመርሃ ግብሩ አመራሮቹ በጅግጅጋ ከተማ አዲስ እየተገነቡ እና ጥገና እየተደረገላቸው የሚገኙ የአስፓልት መንገዶች ያሉበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡
 
በዚህ ወቅትም አቶ ሙስጠፌ የተጀመሩ ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲጠናቀቁ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.