Fana: At a Speed of Life!

ለአሸባሪው ህወሓት በዓለም ዓቀፍ ተቋማት የሚደረገው ድብቅ ድጋፍ ሊያበቃ ይገባል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ካቢኔ አንደኛ አመት የመጀመሪያ ሰብሰባውን በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
 
የአዲስ አበባ የመዋቅራዊ ጥናት ማሻሻያ ላይ በዋናነት መሠረታዊ የህዝብ ጥያቄዎች ለሚነሳባቸዉ ጉዳዮች ትኩረት በመስጠት እና በተለይም በመንገድ ግንባታ፣ በአረንጓዴ ልማት ፣በህንጻ ከፍታ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እና በአጠቃላይ በከተማዋ የፕላን ትግበራዎች ላይ የታዩ ክፍተቶችን ለማረም በሚያስችሉ የመፍትሄ ሀሳቦች ዙሪያ ነው ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈው።
 
በዚሁ መሰረት የከተማ አስተዳደሩ ወቅታዊውን የገበያ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ለሸገር ዳቦ ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች የ309 ሚሊዮን 337 ሺህ 500 ብር ድጎማ እንዲደረግ ወስኗል፡፡
 
የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እህት ኩባንያ የሆነዉ ሆራይዘን ፕላንቴሽንም ለተመሳሳይ ዓላማ የ199 ሚሊዮን 837 ሺህ 500 ብር ድጎማ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
 
ካቢኔው በስብሰባው የተማሪዎች ምገባ የዋጋ ማሻሻያ ሰነድ ላይ ውይይት በማድረግ ለ2014 የትምህርት ዘመን የ1.9 ቢሊዮን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ወስኗል።
 
በተያያዘም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የመዋጮ መጠን እንዲወሰን እና በከተማዋ ከ231 ሺህ በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ዉስጥ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የጤና መድህን ሽፋን አገልግሎት ለመስጠት የ 144 ሚሊየን ብር ድጋፍ በአስተዳደሩ እንዲደረግ ወስኗል።
 
በተመሳሳይ በከተማዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ከ231 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የጤና መድህን ሽፋን አገልግሎት ለመስጠት የ144 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ወስኗል።
 
የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ቡድንን የፋይናንስ አቅም ለማጠናከር የሚያስችል የ70 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲደረግለት ካቢኔ ከውሳኔ ላይ የደረሰ ሲሆን÷የስፖርት ቡድኑ በዘላቂነት ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረዉና በፋይናንስ የራሱን የገቢ ምንጭ መፍጠር የሚያስችለው የተለያዩ አማራጮችን እንዲፈጥር ከውሳኔ ላይ ደርሷል።
 
በመጨረሻም በሀገሪቱ ለተለያዩ አካባቢዎች ለማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማገዝ እና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል ጊዜአዊ ኮሚቴ እንዲዋቀር አቅጣጫ ማስቀመጡን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.