Fana: At a Speed of Life!

ያለንበት ወቅት የዜጎችን ሃላፊነት የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ሚና ሊወጣ ይገባል-አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 20ኛ ዙር ምልምል የፌዴራል ፓሊስ ሰልጣኞች የምረቃ ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት በጦላይ ተካሂዷል፡፡
 
በስነ ስርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የኢትዮጽያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱአለምን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
 
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በምረቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ አሁን ለይ ኢትዮጵያ ታሪካዊ ወቅት ላይ የምትገኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ተመራቂዎችም በዚህ ታሪካዊ ወቅት የአባቶቻችንን ጀግንነት እና አልበገር ባይነት ልትደግሙት ይገባል ነው ያሉት፡፡
 
ያለንበት ወቅት የሁሉንም ዜጋ ሃላፊነት የሚጠይቅ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ደመቀ÷ለዚህም ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡
 
ሀገር የገጠማትን ፈተና ለመመከት ጠንካራ ኢኮኖሚ፣ ጠንካራ መከላከያ ሰራዊት እና ፖሊስ ያስፈልጋታልም ብለዋል፡፡
 
ዛሬ ከተመረቁት ሰልጣኝ ፌዴራል ፖሊሶችም ሀገር ብዙ እንደምትጠብቅና ታሪክን በቁም መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
 
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤልም በበኩላቸው÷ በ20ኛው ዙር የተመረቁ ሰልጣኞች አዲሱን የፖሊስ ዶክትሪን ያካተተ ስልጠና እንደተሰጣቸው ነው የገለጹት፡፡
 
ከዚህ ባለፈም ሀገሪቱን ለማፈራረስ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የጁንታው ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እንደ ሀገር እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት መመረቃቸው ልዩ እንደሚያረገውም አንስተውዋል፡፡
 
የፌደራል ፓሊስን ለማዘመንና የተሻለ አቅም ለማዳበር መንግስት እንደሚሰራ ኮሚሽነር ጀነራሉ ደመላሽ ተናግረዋል፡፡
 
ሰልጣኞችም ሀገራቸውን ለማገልገል ቁርጠኛ አቋም መያዛቸውንናአሸባሪው ህወሓት ሀገርን ለማፍረስ በሚያደርገው ጥረት ያሳደረባቸውን ቁጭት ለመወጣት በከፍተኛ ወኔ መሰልጠናቸውን አውስተዋል፡፡
 
ተመራቂዎች ከስልጠናው የአላማ ፅናት፣ አካላዊ ብቃት ፣ በቂ ክህሎት እና እውቀት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በዘቢብ ተክላይ

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.