Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ እድሳት የተደረገላቸው 69 የአቅመ ደካማ ቤቶች ርክክብ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍል ከተማ ወረዳ 8 በክረምት በጎ ፍቃድ እድሳት የተደረገላቸው 69 የአቅመ ደካማ ቤቶች ርክክብ እየተደረገ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እድሳት የተደረገላቸው የአቅመ ደካማ ቤቶችን አስረክበዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ በዘንድሮው በከተማው 2ሺህ ያህል የአቅመ ደካማ ቤቶችን ለማደስ እቅድ ቢያዝም ልዩ ልዩ ተቋማትን ፣ባለሀብቶችን እና በጎፈቃደኞችን በማስተባበር ከ2 ሺህ 455 ቤቶችን በአዲስ መልክ አፍርሶ በመገንባት ለነዋሪዎች መሰጠታቸውን ገልጸዋል ።

ህዝባችን በአንድነት መተባበረ እና መተጋገዘ የኢትዮጵያውያን መሠረታዊ መገለጫ ነው ያሉት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቀጣይም የበጎ ፈቃድ ተግባራትን በማጠናከር ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በማልማት፣በማጽዳት እና በማስዋብ ሁሉም ጥረት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

አሸባሪው ህውሃት በከፈተው ጦርነት በወሎ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ፣በቦረና ደግሞ በድርቅ ሣቢያ የተጎዱ ዜጎችን እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊቱን ህዝቡን በማስተባበር የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ነጻነት ዳባ ÷በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በባለፉት የክረምት ወራት 270 የአቅመ ደካማ ቤቶች በአዲስ መልክ ታድሰው ለነዋሪዎች መተላለፋቸውን መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.