Fana: At a Speed of Life!

የናይጄሪያ የዲፕሎማቶችና ባለሀብቶች ልዑክ ጅማን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የናይጄሪያ አምባሳደርና የአፍሪካ ህጻናት ተሰጥኦ አግኝ ፋዉንዴሽን መስራችና ፕሬዚዳንት በዶክተር ኢንጂነር ኖዋህ ዳላጂ የተመራ የዲፕሎማቶችና ባለሀብቶች ልዑክ በጅማ ጉብኝት እያካሄዱ ነው።

የልዑክ ቡድኑ አባላት ትናንት ጅማ ሲደርሱ የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ነጂባ አባ ራያ እና የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባ ፊጣ እንዲሁም ሌሎች የከተማው የስራ ሃላፊዎች በአባጅፋር አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድረገውላቸዋል።

በዛሬው እለትም በከተማው የቱሪዝም መዳረሻዎችና የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እየጎበኙ ሲሆን÷የጉብኝቱ ዋና ዓላማም የጅማን ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ለማጎልበትና በጋራ ለመስራት መሆኑ ተገልጿል።

ጎብኚዎቹ ከ150 አመት በላይ ያስቆጠረውን የጅማን ታሪካዊ ሙዝየም በመጎብኘት ባዩት ታሪካዊ ቅርስ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

ዶክተር ኢንጂነር ኖዋህ ዳላጂ “የኢትዮጵያና የናይጄሪያ የቆየን ግንኙነት ለማጠናከር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንሰራለን” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝምና በኢኮኖሚ ለማጠናከር አልመው ወደ ታሪካዊቷ ጅማ መምጣታቸውንም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.