Fana: At a Speed of Life!

በተለያዪ ችግሮች ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ በሀገሪቱ የተለያዪ አካባቢዎች በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጥሪ አቀረበ፡፡
ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ መቋቋም የሚያስችል የድጋፍ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰብዓዊ ዲፕሎማሲና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ዶክተር ሰለሞን አሊ ገልጸዋል።
ባለፉት ሶስት ወራት በሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር፣ በሰሜን ወሎና በደቡብ ወሎ አካባቢዎች በችግር ውስጥ ለሚገኙ ከ150 ሺህ በላይ ዜጎች ምግብ-ነክ እና ምግብ-ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እንዲሁም የመድኃኒትና የአምቡላስ አገልግሎት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በደባርቅ፣ ጎንደር፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴና ሀይቅ ለሚገኙ ሆስፒታሎች የመድኃኒት እገዛ መደረጉንም ገልጸዋል።
ማህበሩ በድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ዶክተር ሰለሞን ጠቁመዋል።
ማህበሩ ድጋፉን የሚያደርገው ከአባላት መዋጮ፣ በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ ያሉ ተቋማትና ግለሰቦች ከሚያደርጉት ድጋፍ መሆኑን ጠቅሰው÷ ኀብረተሰቡ በችግር ውስጥ ላሉ ወገኖቹ የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.