Fana: At a Speed of Life!

በጉራፈርዳ ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የባህላዊ እርቀ ሠላም ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የባህላዊ እርቀ ሠላም ስነ ስርዓት አካሄዱ፡፡
ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና ወደ ቀድሞ ሠላማቸው ለመመለስ የሚያስችል የባህላዊ እርቀ ሠላም ስነ ስርዓት አካሂደዋል፡፡
በእርቀ ሠላም ስነስርዓቱ ከፌደራል፣ ከአጎራባች ክልል፣ ከዞንና ከወረዳ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡
በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፋርዳ ወረዳ በሚገኙ በተለያዩ ቀበሌያት ቀደም ሲል ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በርካታ ነዋሪዎች ለሞትና ለመፈናቀል ብሎም ለንብረት ውድመት መዳረጋቸው ይታወቃል፡፡
የአካባቢውን ማህበረሰብ የቆየ አብሮነት ለማጠናከርና የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የባህላዊ እርቀ ሠላም ስነ ስርዓት አካሂዷል፡፡
የእርቅ ሠላም ስነ ስርዓቱ በአካባቢው ባህል መሠረት የተካሄደ ሲሆን÷ ይህ የእርቀ ሠላም ሂደትም የቆየውን የህዝቦችን የጋራ ማህበራዊ መስተጋብር ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል ሲል የደሬቴድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.