Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት አነሳ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ውሳኔ ማሳለፉን የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
የጉባዔው ጽህፈት ቤት እንደገለጸው÷ የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በወንጀል መጠርጠራቸውን በመጥቀስ ምርመራ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ለጉባዔው ጥያቄ አቅርቧል፡፡
ይህን ተከትሎ የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀረበው ጥያቄ ላይ ተወያይቶ በአዋጅ ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 34 (2) መሰረት የሁለቱንም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ መወሰኑን ከፍህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.