Fana: At a Speed of Life!

“የኦሞ ተፋሰስ የስትራቴጂክ ዕቅድ ፕሮጀክት” የባላድርሻ አካላት ምክክር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው “የኦሞ ተፋሰስ የስትራቴጂክ ዕቅድ ፕሮጀክት” የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ጌትፋም ሆቴል እየተካሄደ ነው።
በውይይት መድረኩ የኢፌዴሪ ተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ባለሙያዎች፤ ከደቡብ ክልል እና ከኦሮምያ ክልል የተወጣጡ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እና የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር መስፍን ቢቢሶ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ፥ከዚህ ቀደም ዩኒቨርሲቲው ከስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስ ልማት ጽ/ቤት ጋር የሥራ ውል ተፈራርሞ የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስ ስትራቴጂክ ዕቅድ በጋራ በመስራት ዕቅዱን እያጠቃለለ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በአሁኑ ጊዜ ዩኒቨርሲቲው የኦሞ ተፋሰስ ስትራቴጂክ እቅድ ከሌሎች ባለድርሻ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ለመስራት ከኢፌዴሪ የተፋሰሶች ልማት ባለልጣን ጋር የሥራ ውል ተፈራርሞ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ገብቶ ሥራውን 40 በመቶ በላይ ማከናወኑንም ዶክተር መስፍን ጠቁመዋል።
ውሃን ማዕከል ያደረገ የተፋሰስ ዕቅድ ቀጣይነት ያለው ዕድገት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲያችን ለፕሮጀክቱ ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል ብለዋል።
ይህ የምክክር መድረክ የኦሞ ጊቤ ተፋሰስ ስትራቴጂክ ስራ የደረሰበት ደረጃ የሚታወቅበት፣ በሚቀርቡ የጥናት ጽሑፎች እና ወደ ፊት ለሚሰሩ ሥራዎች ግብዓት የሚገኝበት በመሆኑ ሥራው የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት በመስጠት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ ላይ ከኢፌዴሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ዶክተር አዳነች ያሬድ፥ በኢትዮጵያ ያለ ውሃ የሚያልቅና የማይተካ መሆኑን ጠቅሰው የውሃ ሀብት ልማትን አቅዶ በአግባቡ መጠቀም ተገቢ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የውሃ ተፋሰሶችን ሳይንሳዊ በሆነ አግባብ በመጠቀም፤ ተቀናጅቶም በማቀድ ህብረተሰቡን ሊጠቅም ፥ ሀገርንም ሊያበለጽግ በሚያስችል መልኩ ጥቅም ላይ ለማዋል ተቀናጅቶ በትብብር መስራት አስፈላጊ ነው ሲሉም ዶክተር አዳነች ገልጸዋል።
በኦሞ ጊቤ ተፋሰስ የስትራቴጂክ እቅድ ፕሮጀክት የባለድርሻ አካላት የውይይት ሰነድ ሼልፍ ላይ የሚቀመጥ ሳይሆን ወደ ተግባር በማስገባት በውጤቱ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበት ተወካይዋ ጠቅሰዋል።
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ፥ የፕሮጀክቱ መሪ እና የከርሰ ምድር ባለሙያ የሆኑት ዶክተር አብርሃም አሻ በበኩላቸው፥ በኦሞ ተፋሰስ ስትራቴጂክ ተፋሰስ እቅድ ይዘት እና ቀጣይ በሂደት በሚተገቡሩ ሥራዎች ላይ የሚያተኩር ሰነድ ቀርቧል።
በቀረቡ የውይይት መነሻ ጽሑፎች ላይ ውይይት በማካሄድ አስተያየት ከተሰጠ በኋላ ወደ ፊት በሚተገበሩ ስራዎች ላይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚሰጥ እንደሚጠበቅ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People Reached
113
Engagements
Boost Post
94
3 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.