Fana: At a Speed of Life!

ወጣቱ በአባቶቹ መስዋዕትነት የተረከባትን ሀገር በክብር ለቀጣይ ትውልድ ማስረከብ አለበት – የኦሮሚያ ክልል ወጣት አደረጃጀቶች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቱ በአባቶቹን መስዋዕትነት የተረከባትን ሀገር በክብር እና በብልጽግና ለቀጣይ ትውልድ ማስረከብ አለበት ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ወጣት አደረጃጀቶች ተናገሩ፡፡

የኦሮሚያ ወጣቶት አደረጃጀቶች ፣የወጣቶች ፌዴሬሽን እና የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኦሮሚያ የወጣት አደረጃጀት ሃላፊዎች በሰጡት መግለጫ÷ ቄሮ እና ቀሬ ትናንት በትግሉ ያገኙትን ድል በቁርጠኝነት መጠበቅ አለባቸው ብለዋል፡፡

እኛም እንደ ወጣት አደረጃጀት የትኛውንም መስዋዕትነት በመክፈል ሀገርን ከጥፋት ለመታደግ ዝግጁ ነን ሲሉ በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

የአሸባሪው ህወሓት እና ተላላኪዎቹ በህዝብ እና በሀገር ላይ አደጋ እያደረሱ ይገኛሉ ፤ የሚያደርሱትን ጥፋት ለመቀልበስ የተጀመረውን ዘመቻ በሙሉ ልብ እንደግፋለን ብሏል የኦሮሚያ ወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር ወጣት አድናን ሀጂ፡፡

ሁሉም ወጣቶች የአከባቢያቸውን ሰላም በንቃት በመጠበቅ የሰላም አምባሳደር መሆን አለባቸው ያለው ደግሞ የኦሮሚያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወጣት አመንቲ ቶላ ነው፡፡

የክልሉ የወጣቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ከድር እንዳልካቸው በበኩላቸው፣ አሸባሪውን ህወሓት እስከመጨረሻው ለማጥፋት ፣ የሀገርን ልኡላዊነት እና ሰላም ለማስጠበቅ ወጣቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት ከመከላከያ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በገመቹ ታሪኩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.