Fana: At a Speed of Life!

ታዋቂ ድምጻውያን በሁርሶ ኮንቲንጀንት ወታደራዊ ማሰልጠኛ የኪነጥበብ ሥራዎቻቸውን አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊያን ታዋቂ አርቲስቶች በራሳቸው ተነሳሽነት “ቅድሚያ ለእናት ሀገር” በሚል መሪ ቃል በሁርሶ ኮንቲንጀንት ወታደራዊ ማስልጠኛ ለ4ኛ ዙር ምልምል ወታደሮች የኪነጥበብ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።
በሰላም ማስከበር ተልዕኮ የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ እንደገለጹት÷ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና ወታደሮች ለአገር የሚከፍሉት ዋጋ ያመሳስላቸዋል፡፡
የኪ ነጥበብ ባለሙያዎችና ወታደርሮች ትስስራቸው ሙያዊ ነው፤ ሁለቱም ለሀገር አንድነት የማይተካ ሚና ይጫወታሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አሸባሪ ቡድኑ ላንለያይ ያጋመደን ኢትዮጵያዊነት እሳት ሆኖ እየበላው ነው ያሉት ኮሎኔሉ÷ኢትዮጵያዊ መሆን በራሱ ጀግንነትና ኩራት እንደሆነ መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ወታደር እንደ አሸባሪው ጁንታ በሀሽሽ የሚዋጋ፣ የእርዳታ እህል የሚቀማ፣ ሰውና እንስሳት ሳይለይ የሚገድል ተቋማትን የሚያፈርስ ሳይሆን አብሮ መብላትን ደግነትንና ላመኑበት አላማ መስዕዋት መሆንን፣ የሀገር ክብር ማሰቀደምን የተማረ ነው ሲሉ የወታደሩን ሥነስርአት አክባሪነት አብራርትዋል።
በዚህ ዝግጅት ላይ አረጋኸኝ ወራሽ፣ ጸጋዬ እሸቱ፣ ግርማ ተፈራ፣ ታደለ ሮባ፣ ማዲንጐ አፈወርቅ፣ ጌታቸው ሃይለማርያም፣ መስፍን በቀለ፣ ግርማ ተፈራ፣ መሰረት በለጠ (ጉምጉም)፣ ጌትሽ ማሞ፣ ማሚላ ሉቃስ ፣ መሳፍንት፣ጥላሁን አወቀና ሌሎች አርቲስቶች የኪነጥበብ ሥራዎቻቸውን ለምልምል ወታደሮቹ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.