Fana: At a Speed of Life!

የሱዳንን የሽግግር መንግስት ህጋዊ መሰረት ለመናድ የሚደረግ ማናቸውንም ሙከራ እናወግዛለን-ኢጋድ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን አሁን ላይ በተፈጠረው ሁኔታ የሀገሪቱን የሽሽግር መንግስት ህጋዊ መሰረት ለመናድ የሚደረግ ማናችውንም ሙከራ በጥብቅ እንደሚያወግዝ የምሥራቅ አፍረካ በይነ መንግስታት የልማት ድርጅት (ኢጋድ) ገልጿል።
 
የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ባወጡት መግለጫ፥ ሱዳን ውስጥ አሁን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ድርጅቱን እንዳሳሰበውና በጥብቅ እየተከታተለው መሆኑን አስታውቀዋል።
 
ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ወገኖች ሁኔታውን በትዕግስት እንዲይዙትም ጥሪ አቅርበዋል።
 
ሱዳን የኢጋድ የወቅቱ ሊቀመንበርና የድርጅቱ ጠንካራ መስራች አባል መሆኗን ያወሳው ተቋሙ÷ የሱዳን የሽግግር መንግስትና ህዝብ ሰላምና ዴሞክራሲን ለማጠናከር ለሚያደርጉት ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነ መግጹን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.