Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ አየር ኃይል እየተወሰደ ያለው ጥቃት የሽብር ቡድኑን በማዳከም ድልን በቀላሉ ለመጎናጸፍ ይረዳል – ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአየር ኃይሉ እየተወሰደ ያለው የአየር ጥቃት የሽብር ቡድኑን እንቅስቃሴ በማዳከም በቀላሉ ድልን ለመጎናጸፍ የሚያበረክት መሆኑን የቀድሞ ጦር አባሉ ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ ተናገሩ።
የአየር ኃይሉ ልክ እንደ ትናንቱ በጠላት ላይ እያደረገ ያለው ጥቃት የሚያኮራ ነው ሲሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡
በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የሽብርተኛው የጦር መሳሪያ ማከማቻና መጠገኛ፣ የስልጠና ቦታዎች፣ ለእኩይ ተግበራት ተጭነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሣሪያዎችና ተቋማት ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች በወታደራዊ ውሳኔ ውስጥ የሚያልፉ ንጹሃንን ትኩረት የማያደርጉ መሆናቸውን ከትናንት ታሪካችንም የምንመለከተው ነው ብለዋል፡፡
በሙያዊ ስነ ምግባር የታነጸው ተቋሙ ኪሳራን በቀነሰ መልኩ የሽብር ቡድኑ ላይ ሙሉ ትኩረቱን በማድረግ ጥቃት እየፈጸመ ያለውን ኢትዮጵያ በንጹሃን ላይ ጥቃት እያደረሰች ነው በሚል የምዕራባውያን የመገናኛ ብዙሃን የተዛባ ዘገባም ተቀባይነት የለውም ነው ያሉት፡፡
በቀጣይም ጦርነቱን በፍጥነት በማጠናቀቅ ሀገሪቷ ፊቷን ወደ ልማት እንድታዞር ጥቃቱ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ነው ያሉት።
በአፈወርቅ ዓለሙ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.