Fana: At a Speed of Life!

“ለእናት አገሬ አይደለም መዝፈን ግንባር ድረስ በመዝመት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ” – ድምጻዊ መስፍን በቀለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገርን አፈርሳለሁ ብሎ ከሚመጣ ማንኛውም ኃይል ለመታደግ አይደለም መዝፈን ግንባር ድረስ በመዝመት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ድምጻዊ መስፍን በቀለ ገለጸ።
ድምጻዊ መስፍን በቀለ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጸው ፥አሁን በኢትዮጵያ የተፈጠረው ጦርነት የውስጥ ጉዳይ ብቻ ሳሆን ጠላቶቻችን እያደረጉ ያሉት የውክልና ጦርነት ነው።
ስለሆነም በፈረሰች አገር ላይ መነጋገር ስለማይቻል “አገሬን አፈርሳለሁ ብሎ ከሚመጣ ማንኛውም ኃይል አይደለም መዝፈን ግንባር ድረስ በመዝመት ለእናት አገሬ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ” ብሏል።
ድምጻዊ መስፍን እንደሚለው፤ በሥራ አጋጣሚ ነዋሪነቱን አሜሪካን አገር ቢያደርግም ከእናት አገር የሚበልጥ የለም ብሎ የቻለውን ሁሉ ሊሰጥ ሁርሶ የወታደሮች ማሠልጠኛ በመገኘት ሠልጣኝ ወታደሮችን በሙዚቃ እንዲበረታቱ ማድረጌ ትንሹ ተግባር ነው ሲልም ገልጿል።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት ወታደር ልጅ ነኝ ያለው መስፍን፥ አባቱ ለእናት አገሩ ከ20 አመት በላይ በውትድርና ሙያው ሲያገለግል በካራማራ ቆስሏል፣ ደምቷልም ብሏል።
በወታደር ሕይወት ውስጥ አለማለፌ ያስቆጨኛል የሚለው ድምጻዊ መስፍን ፥አሁን የአባቴን መስዋዕትነት፣ ገድል እኔም መድገም አለብኝ ሲል ገልጿል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.