Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ በአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአውሮፓ ህበረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን እና በአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ ዶክተር አንቴ ዌበር ጋር ተወያይተዋል፡፡
ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ኢትዮጵያ ስኬታማ ምርጫ በማካሄድ አዲስ መንግስት ለመመስረት በመብቃቷ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ማሻሻያ እንደሚደግፍ እና የሚያከናውናቸውን የልማት ስራዎች አጠናክሮ ለመቀጠል እቅድ እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡
 
በተለይም ህብረቱ ኢትዮጵያን በአየር ንብረት፣ በኢነርጅ፣ በጤና፣ በኮሮና ቫይረስ፣ በመልካም አስተዳደር እና በተለያዩ ዘርፎች ዙሪያ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በተለይም ህብረቱ በአየር ንብረት፣ በኢነርጅ፣ በጤና፣ በኮሮና ቫይረስ፣ በመልካም አስተዳደር እና የግል ተቋማትን በማሳደግ ዙሪያ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ከዚህ ባለፈም የሰብዓዊ እርዳታ ያለምንም ገደብ ለተጎጂዎች እንዲደርስ እና በሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ገልተኛ ምራመራ መደረግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

አቶ ደመቀ በበኩላቸው መንግስት ለተጎጂዎች አስፈላጊውን እርዳታ እንዲደርስ ቁርጠኛ መሆኑን በመግለጽ በዚህ ረገድ እስካሁን የተከናወኑ ስራዎችን አስታውሰዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ መንግስት የሽብር ቡድኑ ህወሓት የሚያደርሳቸውን ጥፋቶች በመቋቋም የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ማሻሻያ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

መንግስት ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች በተመሰረተው አዲስ መንግስት የስራ ሃላፊነት እንዲሰጣቸው ማደረጉንም አንስተዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የሽብር ቡድኑ ህወሓት እየፈጸመ ያለውን የተሳሳተ ተግባር እንዲያወግዝ እና ቡድኑ በአማራ ክልል በወረራ የያዛቸው አካባቢዎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለቆ እንዲወጣ ህብረቱ ጫና እንዲፈጥርም ጠይቀዋል፡፡

ህብረቱ በአማራ ክልል አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያደርግም አቶ ደመቀ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.