Fana: At a Speed of Life!

ናይጄሪያ ዲጂታል ግብይትን በመጠቀም የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆነች

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 16፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ናይጄሪያ ዲጂታል ግብይትን በመጠቀም የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሀገር መሆኗ ተገለፀ፡፡
 
የናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክ የግብይት ወጪዎችን ለመቀነስ እና የፋይናንስ ሥርዓቱን ለማዘመን እና ለማሳደግ የዲጂታል ገንዘብ ግብይት ስርአትን መቀላቀሉን አስታውቋል።
 
የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ናይጀሪያ ዲጂታል የግብይት ስርአትን ለዜጎቿ በማስተዋወቅ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሃገር ሆናለች ብለዋል።
 
የግብይት ስርአቱ በቀጣዮቹ 10 አመታት የናይጀሪያን ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት በ29 ቢሊየን ዶላር እንዲያድግ እንደሚረዳውም ተናግረዋል።
 
ቡሃሪ አክለውም የዲጂታል ገንዘቦች ብዙ ሰዎችን እና የንግድ ስርዓቶችን ከኢ-መደበኛ ወደ መደበኛው ዘርፍ እንዲሸጋገሩ ያግዛል፣ በዚህም የሀገሪቱ የታክስ መሰረቶች ይጨምራሉ ነው ያሉት።
 
ከግብይት ስርአቱ መጀመር በኋላ በ33 ባንኮች ውስጥ ከ 2 ነጥብ 5 ሚለየን በላይ ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን እና ከ1 ነጥብ 2 ሚለየን ዶላር በላይ የገንዘብ ዝውውር ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
 
ምንጭ፦ አልጀዚራ

በሚኪያስ አየለ

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.