Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር አላስታር ማክፋይል ጋር በተለያዩ አገራዊ የልማት ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው በተለይም በአሁኑ ወቅት መንግስት በከተሞች የሚታየውን የሥራ አጥነት፣ የመኖሪያ ቤት ዕጥረትና ከሰላም ጋር በተያያዘ እያደረገ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጥረት በተመለከተ መክረዋል፡፡

አምባሳደር አላስታር ማክፋይል በዚሁ ወቅት መንግስት በቀጣይ 10 ዓመት በከተሞች የያዛቸውን ዕቅዶችን ለመተግበር በሚያደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን መግለፃቸውን ከከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.