Fana: At a Speed of Life!

የማህበርሰብ አቀፍ ጤና መድህን ድጎማ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ በልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የጤና መድህን ድጎማ አድርጓል፡፡

ቢሮው በከተማ ግብርና ፣ በጥቃቅን እና አነስተኛ ፣በንግድ እና በቀን ስራ ለተሰማሩ የህብረተስብ ክፍሎች ነው የጤና መድህን ድጎማ ያደረገው፡፡

የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ÷ የከተማ አስተዳደሩ ከ231 ሺህ በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ29 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጎ በነጻ እንዲታከሙ ማድረጉንም ገልጸዋል ፡፡

በዘንድሮው ዓመት አዲሱ የከተማ አስተዳደር ካቢኔ በመጀመሪያው ስብሰባው ለማህበራዊ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት ለ288 ሺህ እማወራ እና አባወራ 144 ሚሊየን ብር ድጋፍ በማድረጉም አመስግነዋል ፡፡

ህብረተሰቡ ይህንን ከግምትውስጥ በማስገባት የማህበረሰብ ጤና መድህን ምዝገባና እድሳት ጊዜ ከጥቅምት 15 እስከ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በመሆኑ በተጠቀሰው ጊዜ እንዲመዘገቡና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

በሲሳይ ጌትነት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.