Fana: At a Speed of Life!

በከተሞች ፅዳትና ውበት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ተባለ

አዲስ አበበባ፣ጥቅምት 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት የቤቶችና የከተማ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሄኖስ ወርቁ÷ ከተሞች በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና አረንጓዴ ልማት ስራ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ቆሻሻ ሃብት ነው ያሉት አቶ ሄኖስ÷ሚኒስቴሩ ከከተሞች ቆሻሻ ኮምፖስት እንዲመረት በማድረግ ለአረንጓዴ ልማት እንዲውል እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ለዚህም የናማ ኮምፖስት ፕሮጀክት በ6 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር በስድስት ከተሞች ላይ 45 ሺህ ቶን ኮምፖስት ማምረት ተችሏል ነው ያሉት፡፡
ፕሮጀክቱ በሌሎች ከተሞች ላይም ተግባራዊ ይደረጋል ያለው ሚኒስቴሩ÷ ከተማን ፅዱና ውብ ለማድረግ የሁሉም አካል ተሳትፎ ያስፈልጋል ብሏል፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ፅዳትና አረንጓዴ ልማት ላይ ያተኮረ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ነው።

በዘላለም ገበየሁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.