Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በደቡብ ወሎ ዞን ሰርጎ በገባባቸው ስፍራዎች አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በደቡብ ወሎ ዞን ሰርጎ በገባባቸው ስፍራዎች ላይ አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን አስታወቀ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱ ሁሴን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ÷ በሀገር መከላከያ ሰራዊቱ፣ በፌዴራል ፖሊስ ፣ በአማራ ልዩ ሀይል ፣ በፋኖ እና በሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጥምረት አሸባሪው የህወሓት ቡድን አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ መሆኑን ተናግረዋል::

የአሸባሪ ቡድኑን ቀብር ለመፈፀም የሚቆጠብ ጉልበትም ሆነ ገንዘብ አይኖርም በማለትም መላው ማህበረሰብ ቁርጠኛ ሆኖ ሀገር የማዳን የህልውና ዘመቻው ላይ እየተንቀሳቀስ ይገኛል ብለዋል::

የአሸባሪ ቡድኑን ግብአተ መሬት በወሎ ምድር ለመፈፀምም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ርብርብ ሊያደርግ ይገባል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፥ በዚህም በአጭር ጊዜ የህልውና ዘመቻውን በማጠናቀቅ የብልፅግና ጉዟችንን እንቀጥላለን ነው ያሉት::

በአዲሱ ሙሉነህ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.