የቱርኩ ፕሬዚዳንት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የደስታ መግለጫ ላኩ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶኻንለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደስታ መግለጫ ላኩ።
ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን በደስታ መግለጫቸው ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል ።
በቀጣይም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና የህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰሩ በመግለጫቸው ማስፈራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከአሁን በፊት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚያችሉ ስምምነቶች መፈረማቸው ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People reached
784
Engagements
–
Distribution Score
Boost Post
654
109 Comments
21 Shares
Like
Comment
Share