Fana: At a Speed of Life!

ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ ከ 4 ሺህ 700 በላይ ሰዎች በኮቪድ -19 ተይዘዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ ከ 4 ሺህ 700 በላይ ሰዎች በኮቪድ 19 ሲያዙ 227 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለፀ።

ኢንስቲትዩቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው በሳምንቱ 139 ሰዎች ለፅኑ ህመም ተዳርገዋል።

በኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ምክትል ሀላፊ ዶክተር ሚኪያስ ተፈሪ÷ የቫይረሱ ስርጭት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ገዳይነቱ ጨምሯል ብለዋል።

እንደ ሀገር በሳምንት ከሚመረመሩት ሰዎች ከ 10 በመቶ በላይ የሚሆኑት በቫይረሱ እየተያዙ ሲሆን÷ በሳምንቱ እስከ 20 በመቶ በቫይረሱ የተያዙባቸው ክልሎች እና ከተሞች እንዳሉም አሳውቋል።

ሀዋሳ፣ድሬደዋ፣አማራ እና ሲዳማ ክልሎች ደግሞ ስርጭቱ ከፍ እያለባቸው ከሚገኙት ተጠቃሾቹ ናቸውም ብለዋል።

ህብረተሰቡ የመከላከያ መንገዶችን መተግበር እስካልቻለ ድረስም በቫይረሱ ምክንያት በየቀኑ የምናጣቸውና ከሞት ጋር የሚታገሉ ሰዎች ቁጥር ከዚህ ሊብስ እንደሚችልም ተመላክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም እድሜያቸ ከ18 አመት በላይ የሆናቸው ሁሉ በየአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የመንግስት ጤና ተቋማት በመሄድ ክትባቱን መውሰድ እንደሚገባቸውም ዶክተር ሚኪያስ አሳስበዋል።

የህብረተሰቡ መዘናጋት በዚሁ ከቀጠለም የጤና ተቋማት ህሙማንን ማስተናገድ ከማይችሉበት ደረጃ ላይ ከመድረሳቸው በተጨማሪ ሌሎች ህክምናዎች ላይም ጫና የሚፈጥር በመሆኑ ሁሉም ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባልም ተብሏል።

ኢንስቲትዩቱ ቫይረሱን ለመከላከል ተብለው የወጡ ክልከላዎችን እና ፕሮቶኮሎችን ማስተግበር ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የተጠናከር ስራ እንደሚሰራም ዶክተር ሚኪያስ ተናግረዋል።

በዙፋን ካሳሁን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.