Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን እንዲደገፉ ለማስቻል ያለመ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስት የተራድኦ ድርጅቶች በአማራ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን መደገፍ እንዲቻል የአንድ መቶ ሚሊየን ብር በላይ ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል።
የተራድኦ ድርጅቶቹ የተፈናቀሉ ወገኖችን መደገፍ በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ ከአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ እና ከክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር ምክክር በማድረግ ተፈራርመዋል።
የተራድኦ ድርጅቶቹ ይፋ ያደረጉት ፕሮጀክት ከመቶ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበትም ታውቋል፡፡ ለፕሮጀክቱ ገንዘብ አፈላላጊው ኮምፓሽን ኢንተርናሽናል የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑም ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይዎት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ፥ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን እና የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማኅበር ደግሞ የፕሮጀክቱ አስፈጻሚዎች ናቸው ነው የተባለው።
የተራድኦ ድርጅቶቹ አሁን ላይ ከሚያድጉት ደራሽ ድጋፍ በተጨማሪ ተፈናቃዮች በዘላቂነት እንዲቋቁሙ እንደሚሠሩም መገለጹን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.